This Content Is Only For Subscribers
ዛሬ ላይ እንደ አንዲስ መስለው በ ዳርዊን የዝግመተ ለውጥ ጽንሰ ሐሳባ ወይም የ ሕዋ አመጣጥ ሳይንሳዊ ትንተናዎች ላይ የተቀመጡት ጽንሰ ሐሳቦች፤ ምንም እንኳን የዘመኑ የምርምር ውጤቶች ቢመስሉም ነገር ግን በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ አዲስ ነገር አይደለም። ይህ የቁሳዊ ፍልስፍና ትንተና የዛሬ 2500 ዓመታት በፊት ሲንጸባረቅ የነበረ ሐሳብ ነው።
በዘመኑ ይኖሩ የነበሩ የፍልስፍና አስተማሪዎች በከፈቱት ትምህርት ቤት ከፍልስፍናቸው መካከል ስለ ፍጥረት አመጣጥ እና የሕዋ አጀማመር ትምህርቶችን ያስተምሩ ነበር። ይህ ትምህርት ቤት ሚሌዥያን ትምህርት ቤት ሲባል የተከፈተው ከ ክርስቶስ ልደት በፊት በ 6ኛው ምዕተ ዓመት ነበር። ቴልስ እና አናክሲማንደር ሰዎች ከእንስ ሳት በዝግመተ ለውጥ እንደመጡ እንስ ሳት ደግሞ ከዕጸዋት ዕጽዋት ደግሞ ከኢንኦርጋኒክ ኢለመንቶች በሂደት እንደመጡ እና ለሁሉም መነሻ ደግሞ የውሃ አካል እንደነበር ያስተምሩ ነበር። ይህ የዘመኑ የሳይንስ ውጤት ከተባለው የዝግመተ ለውጥ ጽነሰ ሀሳብ ከጥቂት ማሻሻያዎች በስተቀር በመሰረታዊ ሐሳቦቹ እጅጉን የሚስማማ ሆኖ እናገኘዋለን። ዜኖፌንስ ድግሞ በደረቅ መሬት የሚመላለሱ እንስ ሳት በውሃ አካላት ውስጥ ከሚኖሩ እንስ ሳት በዝግመተ ለውጥ ሂደት እንደተገኙ ያስተምር ነበር። ለዚህም ማስረጃው የሼል ቅሪተ አካል በውሃ አካላት ወለል ላይ ሊገኝ ሲገባ በተራሮች ጫፍ ላይ ማግኘቱን በማሳየት ነበር።ሄራክሊተስ እና ኢምፔዶክልስ ደግሞ በ አካል ላይ የሚከሰቱ የዘፈቀደ ለውጦች አዳዲስ ፍጥረታቶችን እንዳስገኙ ዳርዊን ገና ሳይጽፍ ከረጅም ዓመታት በፊት አስተምሮ ነበር።
ዛሬ በዓለማችን ላይ በተለይም በምዕራቡ ዓለም ላይ ተንሰራፍቶ ያለው የዝግመተ ለውጥ ፍልስፍና ያኔ በጥንት ዘመን በግሪክ ፍልስፍናዎች ላይ መነሻውን ማየት እንችላለን።ነገር ግን ቴልስ በመጀመርያ እነዚህን ትምህርት ሲያስተምር አስቀድሞ ከራሱ የፈለቀ አልነበረም። የግሪክ አፈታሪኮች እና የሌሎች ህዝቦች አፈታሪኮች ከላይ ለተነሱት ፍልስፍናዎች መነሻ ወይም ግብዓት ነበሩ።
በምስራቁ የዓለማችን ክፍል ከነበሩት ቀደምት ፈላስፋዎች መካከል ኮንፊሺየስ ተጠቃሽ ነበር። ይህም ፈላስፋ ኮንፊሺየዚኒም ተብሎ የሚጠራ የዕምነት፨ሐይማኖት መስራች ነበር።
“ከምዕራቡ ዓለም ስናነጻጽር ፣ የሩቅ ምስራቅ ፈላስፋዎች ስለ ፍጥረት አመጣጥ በዝግመተ ለውጥ ነጥቦች መሰረት ያስረዱ ነበር። . . . በጣም የሚገርመው የዚያን ዘመን ፈላስፋዎች የፍጥረትንም ሆነ የሕዋን አነሳስ ከፍጥረት በላይ በሆነ ፈጣሪ ወይም ነዳፊ ጋር አለማያያዛቸው ነበር ”
Ilza Veith, “ Creation and Evolution in the Far East” p.2
“ ከመጀመርያው ጀመሮ የቻይና ፈላስፋዎች በፍጥረት ላይ ከሌላው በጣም የተለየ አመለካከት ነበራቸው። ከእነዚህ መካከለም ህዋ በራሱ የተፈጥሮ ሂደት አሁን ወዳለበት ደረጃ እንደ ደረሰ. . .”
David L. Johnson, A Reasoned Look at Asian Religions.
በመሆኑም የዝግመተ ለውጥ ጽነሰ ሐሳብም ሆነ የሕዋ አመጣጥ ትንታኔዎች እንደሚባለው የዘመኑ የሳይንስ ቱሩፋቶች ሳይሆን ቀድሞም የነበረ ፍልስፍና ነበር።