- Advertisement -Newspaper WordPress Theme
ስነ ፍጥረትሶሻል ዳርዊኒዝም

ሶሻል ዳርዊኒዝም

ዳርዊን በ “Descent of Man” መጽሃፉ ( በመጀመርያ የታተመው የካቲት 24 1871 )የተፈጥሮ አመራረጥ ሀሳብ በሰው ልጆች ማህበረሰብ ላይም መመልከት እንደሚቻል ገልጿል። የሰለጠኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ችግረኛ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመርዳት የሰው ልጆች ዘርን ጎድተዋል ብሎ ያምን ነበር። ይህንንም ሲያስረዳ ተፈጥሮ በራሷ ልታስወግዳቸው የፈለገችውን ደካማ ፣ታማሚ እና ችግረኛ ማህበረስቦችን በህይወት እንዲቆዩ መርዳት ያንን የተፈጥሮ ህግ መጣስ አግባብ አይደለም ሲል ተናግሯል።

በዚህም የተነሳ ዳርዊን እንዲህ አይነቱ የድጋፍ እና እገዛ ሰብዓዊ አገልግሎቶች ቀስ በቀስ የሰውን ዘር ከምድረገጽ ሊያጠፋ ይችላል ብሎ ያምን ነበር። ይህም ብቻ ሳይሆን ወደ ፊት ብርቱ የሆኑት የማህበረሰብ ክፍሎች ደካማ የሆነውን ማህበረሰብ ከምድረ ገጽ ያጠፋሉ ሲል ተንብዯል።

“ወደፊት ብዙም ሳይርቅ የሰለጠነው የሰው ልጅ ማህበረሰብ ደካማ እና እንስሳዊ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ከምድረገጽ እንደሚያጠፋ እና እንደሚተካቸው እርግጠኛ ነኝ”

 ቻርለስ ዳርዊን , “The descent of man” ምዕራፍ 6 “Affinities and Genealogy” ገጽ 201

ምንም እንኳን ዳርዊን ይህ ምን ዓይነት ተጽዕኖ ሊፈጠር በመገንዘቡ የመወዛገብ ስሜት ቢሰማውም ነገር ግን ይህ ጽንሰ ሐሳብ በጀርመን የተነሱ አዳዲስ ፖለቲከኞችንና ሳይንቲስቶችን የሓሳብ ፍልስፍና ሰጥቷቸው ነበር።

ይህም አዲስ እውቀት ወደፊት የበላይነትን ለማስገኘት ለሚደረጉ ማንኛውም ድርጊቶች(ጦርነት፣ግድያ፣መሬት ወረራ፣ቅኝ ግዛት እና የመሳሰሉት) እንደ ስነሕይወት መሰረት ተቀባይ መሆኑን የሚያረጋግጥ አስተሳሰብ ነው። ይህ በእርግጥ በጣም አደገኛ አስተሳብ ነበር።

“በወቅቱ የነበሩትን ሳይንቲስቶች ስንመለከት በ አብዛኛው በሚባል ደረጃ ዘረኝነትና ፣ዘር የማጽዳት ተግባር እንዲሁም የሌሎችን መሬት እና ሀብት መቀማትን የሚደግፉና የሚያበረታቱ ነበሩ።” ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዊካርት(ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ )

“የመጠፋፋት ጦርነት. . . የተፈጥሮ ህግ ነው. . . ህይወት ያላቸው ፍጥረታትም እስካሁን ሊቀጥሉ የቻሉት በዚሁ ነው ” ጀርመን ዚኦሎጂስት ጉስታቭ ፌይገር (1870)

“ለመኖር የሚደርግ ትግል ለዝግመተ ለውጥ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ሁሉ . . . በሰው ልጅም ታሪክ የደካማ ህዝቦች በሰለጠኑ ሕዝቦች መደምሰስ አንዱ የለውጥ ባህርይ ነው።” ጀርመን ኢትኖሎጂስት ፍሬድሪክ ሄልዋልድ (1875)

“እንደዳርዊን ጽንሰ ሐሳብ መሰረት ከሆነ፣ ጦርነት ለሰው ዘር እደገት ከፍተኛ ሚና አላው። ይህም ሲባል በ አካል ደካማ የሆነውን፣ ደካማ አስተሳሰብ ያለውን እና በሞራል ያነሰውን ለሰለጠነውና ለጠንካራው ማህበረሰብ ቦታ መልቀቅ አለባቸው። “ ጀርመን የስነ ህይወት ተመራማሪ ሄይንሪክ ዚግለር, “Naturwissenschaft” ገጽ 167, 1893

የዳርዊኒስቶች በወቅቱ በዝግመተ ለውጥ ሂደት ውስጥ በዝቅተኛ የለውጥ ደረጃ ላይ የሚገኙት ተብሎ በሚታሰቡት የሰው ዘሮች ላይ ጦርነትና ቅኝ ግዛትን አበረታተው ነበር።

ለምሳሌ በ አፍሪካ የሚኖሩ ማህበረሰቦች ላይ የተደረገውን እንመልከት። በደቡብ ምዕራብ አፍሪካ የምትገኘው የ አሁኗ ናሚብያ ተብሎ የሚጠራው ምድር በጀርመኖች ቅኝ ግዛት ስር ነበር።የሶሻል ዳርዊኒዝም አመለካከት የነበራቸውና በወቅቱ ያን አካባቢ በቅኝ ግዛት የያዙ የጦር ሰራዊት አዛዦች ሶሻል ዳርዊኒዝምን በዚያ ምድር በሚኖሩ ማህበረሰቦች ላይ ተግብረውታል።

ይህም በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እጅግ ክፉና አሰቃቂ ሆኖ አልፏል። “ጀርመናውያን በዚህ የሚገኙትን ማህበረስቦች ከሞላ ጎደል እንደ ዝንጀሮ መሰል እንስ ሳ ነው የሚያዩዋቸው” የጀርመን ሚሽነሪ በ አፍሪካ ከ1904 እስከ 1908 የጀርመን ጦር ሰራዊት በ አካባቢው ይኖሩ የነበሩትን ሄሬሮ የተባሉ ማህበረሰቦችን ከ ደቡብ ምዕራብ አፍሪካ ምድር ለማጥፋት ሞክረው ነበረው።

አንዳንድ የታሪክ ሊቆችም ይህንን ክስተት የ20ኦናው ክፍለዘመን የመጀመርያው ዘር ጭፍጨፋ ሲሉ ይኮንኑታል። በጥቅምት 2, 1904 ጀነራል ሎታር ቮን ትሮዛ የዘር ማጥፋት ስራውን አስጀመረ። የሰጣቸው ምርጫ ቢኖር አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አልያም ግድያ እንደሚጠብቃቸው አወጀ።የሄረሮ ወንዶች ግድያ ሲፈጸምባቸው ሴቶችና ልጆችን ደግሞ በ አከባቢው ባለው አሸዋማ በርሃ እንዲሞቱ ለጥም እና ረሃብ አሳልፎ ሰጣቸው። ጀነራል ቮን ትሮዛ ይህንን ምግባሩን በሶሻል ዳርዊኒዝም አማካኝነት ተቀባይነት ያለው መሆኑን ደጋግሞ ያስረዳ ነበር።

በወቅቱ ለነበረ ጋዜጣም የሰው ልጅ ለደካማው ያለ ርህራሄ የዳርዊንን ለመኖር የሚደረግ ትግል የሚለውን ህግ ሊያስቀር አይችልም ሲል ተናግሯል። በኋላም በጀርመን ከ አንዳንድ ማህበረሰብ ክፍሎች ተቃውሞ ሲደርስበትም ይህንን ተግባሩን በሌላ መንገድ ቀጠለ። በቀጥታ ከመግደል ይልቅ ወደማጎሪያ ማዕከል በማስገባት በበሽታ እንዲያልቁ አደረገ። አንዳንዶቹንም ለህክምና በህይወት እንዳሉ ይመራመሩባቸው ነበር። ከሞቱት መካከልም የራስ ቅል አጽማቸውን ወደ ጀርመን በመላክ የዘር ጥናት በሚያጠኑ ተመራማሪዎች ጥናት ይደረግ ነበር። በ1908 80 መቶ የሚሃሉ የሄሬሮ ማህበረሰቦች በዘር ጭፈጨፋው እንዳለቁ ይታመናል።

Subscribe Today

GET EXCLUSIVE FULL ACCESS TO PREMIUM CONTENT

SUPPORT NONPROFIT JOURNALISM

EXPERT ANALYSIS OF AND EMERGING TRENDS IN CHILD WELFARE AND JUVENILE JUSTICE

TOPICAL VIDEO WEBINARS

Get unlimited access to our EXCLUSIVE Content and our archive of subscriber stories.

Exclusive content

- Advertisement -Newspaper WordPress Theme

Latest article

More article

- Advertisement -Newspaper WordPress Theme