- Advertisement -Newspaper WordPress Theme
ሥነ-ህይወትየሞት ደርሶ መልስ ክስተቶች

የሞት ደርሶ መልስ ክስተቶች

ዶክተር ሜሪ ኒል በእረጅም እና አድካሚ የትምህርት እና ልምምድ ጊዜ አሳልፋ በአጥንት ቀዶ አካሚነት ስራዋን የምትሰራ ሴት ነበረች::

ሳይንቲስት ነኝ …ከየትኛውም የእምነት ወይም መንፈሳዊ እውነታ ይልቅ ሙሉ ለሙሉ ለሳይንስ ህይወቴን የሰጠሁ ሰው ነበርኩ:: . . .ወይ ሳይንስ አልያም ሃይማኖት ለሚለው ምርጫ ለሳይንስ በመወገን ሁለቱ አብረው ሊሄዱ የማይችሉ መሆናቸውን አምን ነበር::

ዶክተር ሜሪ ኒል

ዶክተር ሜሪ በዚህ የትምህርት እና ተመራማሪነት ውስጥ በማለፏ በሞት የደርሶ መልስ ታሪኮች ላይ ተጠራጣሪ የነበረ አቋም ነበራት:: በእረፍት ጊዜዋ በደቡብ አሜሪካ ቺሊ በሚባል ሃገር በሚገኘው ወንዝ ውስጥ እየተንሳፈፈች ለመዝናናት ተዘጋጅታ ጉዞዋን ወደዚሁ ቦታ አቀናች:: ነገር ግን ትዝናናበት የነበረው አነስተኛ መንሳፈፊያ በድንጋይ ውስጥ በመያዙ ከ 2.5ሜትር ጥልቀት ባለው ውሃ ውስጥ ተይዛ ለ30 ደቂቃዎች ቆየች::

በቦታው የደረሱ የነፍስ አድን ባለሙያዎች ሰውነቷን ወንዙ ተፍቶት በወንዙ ዳር ስላገኙት የሚችሉትን ያህል ህክምና ካደረጉላት በኃላ ከከባድ የሰውነት አደጋ ጋር ተመልሳ በሕይወት ለመኖር በቅታለች:: በዚያች ሞትን በቀመሰችባቸው ደቂቃዎች የሆነችውን ትናገራለች::

እንደ ዊኪ ፒዲያ መረጃ ይህ የ’ሞት ደርሶ መልስ ተሞክሮ’ ጉዳይ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ሲነገር የነበረ ቢሆንም እ.ኤ.አ ከ1890ቹ ጀምሮ በፍልስፍና እና በስነ-ልቦና ተመራማሪዎች ሲጠና የነበረ ጉዳይ ነው:: ነገር ግን በተለይ በ1960ቹ የተለየ ትኩረት ሲሰጠውና ሲጠና ቆይቷል:: በ2011 በወጣው የኒዎርክ ሳይንስ አካዳሚ አመታዊ ዘገባ በሰሜን አሜሪካ ግዛት ብቻ ወደ 9ሚሊዮን የሚደርሱ የሞት ደርሶ መልስ ባለታሪኮች መኖራቸውን አስታውቋል::

በሚሊዮን የሚቆጠሩ እነዚህ ባለታሪኮች ወይም ግለሰቦች ምንም እንኳን ከተለያየ የዓለም ክፍል ከተለያየ የሃይማኖትና ባህል እንዲሁም ከተለያየ የእድሜ ክልል የተወጣጡ ቢሆንም ተመሳሳይ የተሞክሮ ታሪክ እንዳላቸው ጥናቶች ይመሰክራሉ:: ይህም ለጉዳዩ የተለየ ትኩረት እንዲሰጠውና እንዲጠና እድሉን ከፍ አድርጎታል::

እነዚህ የደርሶ-መልስ ታሪኮች በተመሳሳይ መልኩ በዋናነት:-

  1. እንደሞቱ ማወቅ/መገንዘብ
  2. ከምንም አይነት ህመም ነፃ መሆንና ደስተኛነት ከሰላም ጋር
  3. ከእራስ ሰውነት ወጥቶ እራስን የመመልከት ሁኔታ
  4. በጠባብ ክፍል መገኘት እና ወደላይ ወይም ወደታች በፍጥነት የመውጣት ወይም የመውረድ ስሜት
  5. የብርሃን ፍንጣቂ ማየት ወይም ወደምትያስደንቅ ብርሃን ውስጥ መግባት
  6. የብርሃን ፍጥረታት ወይም ደግሞ ቀድሞ የሞቱ የቤተሰብ አባላትንወይም ጏደኞችን የመገናኘ ዕድል ማግኘት
  7. የህይወትንሙሉ ቆይታ እንደፊልም መመልከት
  8. ወደፊት ለመሄድ ወይም ወደኃላ ለመመለስ ትእዛዝ መቀበል/በመካከልም ለመሻገር ወይም ወደፊት ለመሄድ መታለፍ ያለበት ክልል ወይም አጥር እንዳለ ማወቅ
  9. ወድ ስጋ ዳግመኛ ተመልሶ የመግባት ወይም የመምጣት ሁኔታዎችን ያካተቱ ናቸው::

ዶክተር ሜሪ ኒል ስለሆነው ነገር እንደዚህ ትናገራለች:: “ከውሃው ውስጥ በህይወት እንደማልወጣ ስለተረዳሁ እና ትንፋሼንም መቆጣጠር እንደማልችል ሳውቅ በቃ ይሄው ነው ብዬ አስቤ በቃ አምላክ ሆይ ፈቃድህ ይሁን ብዬ ፀለይኩ::

በእግዚአብሄር መኖር የማምን ሰው ብሆንም ይንን ያህል እግዚአብሄር በህይወቴ አስፈላጊ አይደለም ብዬ ማስብ ሰው ነበርኩ:: ነገር ግን በነዚያ ቅፅበት ሰከንዶች ውስጥ ከልቤ እና ከእውነት በቃ የሆነው ሆኗል ግን አንተ ሁሉን ተቆጣጠረው ብዬ በእግዚአብሄር ላይ ሁሉንም ተውኩት:: በጣም እንደምሰቃይ እና ሁሉም እንደሚያበቃ ነበር እየጠበኩ የነበርኩት:: ነገር ግን የሚገርም ሰላም እና እረፍት ይሰማኝ ጀመረ:: በእግዚአብሄር እጅ እንደተያዝኩ ገብቶኝ ነበር:: ልክ የአንድ አዲስ ህፃን ትናንሽ ጣቶች ሰው ሲይዝ በአንድ ጊዜ በንፁህ ደስታ ተስፋ እና ፍቅር እንደሚወረስ እንደዚያ እየተሰማኝ ነበር እራሴን ያገኘሁት:: ነገር ግን እኔ ነበርኩ አዲሱ ህፃን:: ጠንቅቆ እንደሚያውቀኝ እንደሚወደኝ እና እንደተቀበለኝም አውቄ ነበር” ::

መንፈሷ ከስጋ ሰውነቷ በቅፅበት ሲለይ እና ከወደላይ ሆና ወንዙን እና ጏደኞቿን ትመለከት እንደነበረ እንዲሁም ጏደኞቿ እና የነብስ አድን ባለሙያዎቹ ዳግመኛ መተንፈስ እንድትችል ሲያደርጉት የነበሩትን ሙከራ ሁሉ በ አየር ላይ ከስጋዋ ውጪ በመሆን ተንሳፍፋ ትመለከት እንደነበረ ትናገራለች::

“በመቀጠልም ብርሃንን የለበሱ ሰዎች ከበቡኝ ደግሞም ይዘውኝ በሃይል ወደላይ ወጡ::የወሰዱኝ ቦታ ምድር ላይ በሌሉ ውብ ቀለማት ይተዋበ ቦታ ነበር:: በምድር ላይ የኖርኩትን ኑሮ ከህፃንነቴ ጀምሮ ያሳለፍኩት ደግም ሆነ ክፉ እንደ ፊልም ሆኖ ይታይ ነበር::ነገር ግን እንደእኔ ብቻ ሳይሆን በነዚያ ሁሉ የህይወቴ ጊዜያት በህይወቴ ውስጥ ተካተው የነበሩ ሰዎች ሁሉ ስሜት እንደራሴ ሆኖ ይሰማኝ ነበረ እና በጣም አሁን ላይ ያለኝ ህይወት እንዲለወጥ ምክንያት ሆኖኛል::” “ምንም እንኳን እዛው መቆየት ብፈልግም ‘አሁን ጊዜሽ አይደለም በምድር የምትሰሪው ስራ አለ’ በማለት በዚያ ውብ እና በፍቅር የተገነባ ቦታ እንዳልቆይ ከለከሉኝ:: ቀጥሎ በጣም በህመም ውስጥ ሆኜ በስጋ አካሌ ውስጥ እራሴን አገኘሁት::”

ምንም እንኳን ትልቅ ቁጥር ያለው የሞት ተሞክሮ ታሪክ ከዓለም ዙርያ ቢመጣም ሳይንስ እስካሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቀ እና ተቀባይነት ያለው ተሞክሮ ነው ለማለት እልደፈረም:: ነገር ግን ይህ ተሞክሮ ከሰላሳ አመታት በላይ በተደረጉ በተለያዩ ጥናቶች ድምዳሜ መሰረት ማንንም ሊያሳምን የሚችል እውነታ እንዳለው መረዳት ይቻላል:: መቼም ይህ የሰው ህይወት እንዲሁ ከሞት በኃላ መሄጃው ማይታወቅበት ጠፍቶ ከንቱ ሆኖ ይቀራል ብሎ ማመን የፈጣሪን አርቆ አሳቢነት እና ጠንቃቃነት እንደመጠራጠር ሆኖ ቢቆጠር አያስደንቅም:: ምክንያቱም የሰው ልጅ እንኳን ብዙ ነገሮችን በብዙ ጥበብ ሲሰራ ብዙ እቅዶችን በውስጡ ይዞ ይሰራል:: ብዙ ታሪኮች አሉ:: በሚቀጥለው የፅሁፍ ልጥፍ ማንበብ ይችላሉ::


Jeffrey Long, MD with Paul Perry “Evidence of the after life”(200-202)

https://www.womansworld.com/posts/comfort/near-death-experience-mary-neal#

Subscribe Today

GET EXCLUSIVE FULL ACCESS TO PREMIUM CONTENT

SUPPORT NONPROFIT JOURNALISM

EXPERT ANALYSIS OF AND EMERGING TRENDS IN CHILD WELFARE AND JUVENILE JUSTICE

TOPICAL VIDEO WEBINARS

Get unlimited access to our EXCLUSIVE Content and our archive of subscriber stories.

Exclusive content

- Advertisement -Newspaper WordPress Theme

Latest article

More article

- Advertisement -Newspaper WordPress Theme